top of page

አይ እቺ አለም

  • Mati(ሙዳሱጣ ዘመካነ ቅዱሳን)
  • Dec 30, 2016
  • 1 min read

painting by ye sheger painter(Emnet)

more of my works will be under this category

በሠመመን ሆኜ፣ ትንፋሽዋ ቢጠራኝ፣ ድብቅ ፈገግታዋ፣ጥሪዋ ቢሠማኝ፣ ብእሬን እንስቼ ሸራዬን እያየሁ፣... አይቻልም ብዬ በቀለም ተቀኘሁ። አይቻልም ውበትዋ፣ ፍጡር አማለለች፣ በፍቅር አናውዛ እያስኮበለለች፣ ደስታ ፈገግታ እልልታን ታውቃለች። ቂም እንደሆን እስዋ አታውቅ፣የትስ ተምራለች? ዘርታ ተከምራ እጥግባ ሸኝ ነች፣ ሰርግንም ለቅሶንም ያውም በአንድ ጀንበር ታስተናግዳልች። አይ እቺ አለም ምስኪን........ ወይ አንድ ፊት የላት አንድ ስሜት አታውቅ ድብልቅ ልቅ ልቅ ልቅ ናት። ደግሞም አይናማ ናት፣ አንዱን በሞት ጥሪ ታባብለው እና፣ አፍዋን ከፍታ ውጣ፣ ባለተራ ጥሪ ከአንገትዋን ቀና። ደሞ አለማፈርዋ ከነክንብንብዋ ነጠላ ዘቅዝቃ ለቅሶ ተቀመጠች፣ አይ እቺ አለም ከንቱ፣ መልከኛ ገዳይ ነች፣ እውነትም እቺ አለም መልከኛ ገዳይ ነች፣ ተውባ እየታየች፣ ስንቱን በአንደበትዋ ገደለች።

~ሙዳሱጣ ዘመካነ ቅዱሳን~


 
 
 

Comments


Featured Posts
Recent Posts
Archive
Search By Tags
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square

© 2016 by Habesha Youth Artists. Proudly created with Wix.com

bottom of page