የጨረቃ ጩኸት
- ጌታይመስገን በላይ
- Dec 30, 2016
- 1 min read

ቀና ብዬ ሳይ፣... በላይ በሠማይ፣ በኩዋክብት ደምቃ፣ አምራና ተውባ፣ ጨረቃ ሹክ አለችኝ፣ በንፋስ ሹክሹክታ፣ እንተ ብቻ እንደሆንክ፣የፍጥረታት ጌታ። የአሠራሯን ተአምር፣የውበትዋን ሚስጢር፣ ለሠው ልጆች ሁሉ ስምህን ልትዘክር፣ ፀሐይዋ ስትጠልቅ ተራዋን ጠብቃ ለዓለም ተገለጠች፣ ምሽቱን ልትቀድስ የቀረኝ እያለች።
~~ ጌታይመስገን በላይ~~
more of my works will be under this category
Comments